face

ወደ ደስተኝነት የሚያደርስ መንገድ ወደ መነሻ መሰረቶቹ ልንመልሳችሁ ወደድን። ሎጂካዊ አስተሳሰብን አብረን በመቅዘፍ በፈላሰፎችና ርእዮተኞች አባባሎች መጠቀምም ፈለግን። የደስተኝነትንና የመታደልን መንገድ ለመፈለግ በምናደርገው ጉዞ በታላላቅ መሪዎች፣በጎምቱ ሰዎችና በታዋቂ ጥበበኞች ተሞክሮዎች መታገዝንም አስፈላጊ ሆኖ አገኘን። ጉዞው የመታደልና ወደዚያ የሚወስድ ርእዮታዊ የስልጣኔ ጉዞ ነው።

በሰው ነፍስያ ድብቅ ባህር ከውስጥ የሚቀዘፍ፣ታሪክንና ያለፈውን ሁሉ የሚያስስ፣መጻኢውን ጊዜ ከሩቅ አሻግሮ የሚመለከት ጉዞ ነው። ሁሉም ወደ መታደልና ወደ ደስተኝነት የሚያደርስ መንገድ ባለቤት ነን በሚሉ የተለያዩና እጅግ በበዙ የርእዮትና የእሳቤ ጎራዎች ማእበል ውስጥ . . ስነልቦናን ጠግነን ለግለሰብ ትኩረት በመስጠት፣ሕብረተሰቦችና ሕዝቦች የመታደልንና የደስተኝነትን መንገድ ለመተዋወቅ ካላቸው ፍላጎት ጋር አብረን ለመጓዝ እንሠራለን . . እናም መንገዱን ለመምረጥና ለመተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ለመሞከርና ለመመዘንም ጭምር፣ተገቢው መስፈርት የቱ እንደሆነ ለማየት ከእኛ ጋር ሁኑ እንላለን . . የመታደልን መንገድ ለመፈለግ የሚደረግ ጉዞ . .

የስነምግባር፣የሳይንስ፣የስልጣኔ፣የርኅራሄና የክብር መንገድ ነው . . እርስዎስ ይህን መንገድ ያውቃሉ . . ?!

ለማወቅስ ይፈልጋሉ . . ?!

የፕሮጄክቱ አሃዶች ወደ ደስተኝነት የሚያደርስ መንገድ የደስተኝነት ውይይቶች መታደልን ፍላጋ . . አደናጋሪ ጥያቄዎችና የሕይወት ፍልስፍና ልቦለድ ድረ ገጹ ከ 21 የሚበልጡ ቋንቋዎችን ይጠቀማል ፦ (ዐረብኛ፣እስፓንኛ፣እንዶኔዝይኛ፣ፋሪሲ፣ሀውሳ፣እንግሊዝኛ፣ቡርቱጋልኛ፣

ጣጂክኛ፣ቤንጋልኛ፣ፊሊፒንኛ፣ፈረንሳይኛ፣ቱርክኛ፣ሩስይኛ፣አማርኛ፣ህንድኛ፣ጀርመንኛ፣ቻይንኛ፣ኡርዱ፣ሰዋሕሊኛ፣ጣሊያንኛ፣ታሚልኛ)። እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ የሆነ ድረ ገጽና የማሕበራዊ ሚዲያ ገጽ አለው።

የእያንዳንዱ ቋንቋ ድረ ገጽ የሚከተሉትን ያካትታል ፦ በመቶዎች የሚቆጠሩ የማብራሪያ ምስሎች። ከ 500 የሚበልጡ የሚታዩ ይዘቶችን ያቀፈ የቪዲዮ ላይብራሪ። ከ 300 የሚበልጡ ይዘቶች ያሉት የድምጽ ላይብራሪ። ከ500 በላይ መጽሐፎችን የያዘ ላይብራሪ። ወደ ድረ ገጹ ይዘቶች ወዳጆችዎን መጋበዝና ማሳተፍ መቻል። አዳዲስ ነገሮች ሲኖሩ በኢሜይል አድራሻዎ ሊደርስዎት መቻሉ። ከተለያዩ ማሕበራዊ ድረ ገጾች በድረ ገጹ ኦፊሻል ገጾች ላይ መሳተፍ መቻሉ። የድረ ገጹ አወቃቀር ግልጽ፣ይዘቶቹም እርስ በርስ የተያያዙ መሆናቸው።