face

ሃይማኖት ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሆኑ

ሃይማኖት ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሆኑ

ሃይማኖት ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሆኑ

ለሰው ልጅ ሃይማኖት ያስፈልገው ይሆን??

www.aroadtohappiness.com

አይንሽታይን

የፊዚክስ ሊቅ
ጠንካራው ውጤት
‹‹እምነት ከሁሉም ጠንካራውና በጣም ውዱ የሳይንሳዊ ምርምሮች ውጤት ነው››

ሃማኖት የግድ ነውን?

የሰው ልጅ በምንም ዓይነት ያለ ሃይማኖት መኖር አይችልም።

የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከሕብረተሰቡ ተነጥሎ ለብቻው መኖር የማይችል ማሕበራዊ ፍጠር እንደሆነ ሁሉ፣በተፈጥሮው ያለ ሃይማኖት ትክክለኛ የሆነ ጤናማ ሕይወት መኖር የማይችል ፍጡር ነው። ስለዚህም ሃይማኖተኝነት ለሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የሆነ ባሕርይ ነው።

የሰው ልጅ ሲጨነቅና መከራ ሲገጥመው ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ተመልሶ የሚማጸነው ከመሆኑ የበለጠ ማስረጃ የለም።አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም፣አላህን፣መግገዛትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ያጠሩታል፤ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ጋራሉ።››[አል ዐንከቡት፡14]

አንድን ዕቃ የሚሰራ ወገን ዕቃውንና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ከማንም በላይ እንደሚያውቅ ሁሉ፣ፈጣሪ አምላክ ስለ ፍጡራኑና አስፈላጊያቸው ስለሆኑ ነገሮች ሁሉ ከማንም በላይ ያውቃል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ውስጥ አዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን።››[አልሙልክ፡14]

www.aroadtohappiness.com

ዴል ካርኒጄ

አሜሪካዊ ደራሲ
ሃይማኖተኛና ሕሙማን
‹‹ሰዎች ስለ ሳይንስና ሃይማኖት መራራቅ እንጂ ሌላ ነገር የማያወሩበት ጊዜ ትዝ ይለኛል። ይህ ክርክር ግን ላይመለስ አብቅቷል። በጣም አዲስ የሆነው የስነልቦና ሕክምና ሳይንስ በሃይማኖት መርህ ያበስራል፤ለምን?! የስነልቦና ሐኪሞች ጠንካራ እምነት፣ሃይማኖትና ጸሎትን አጥብቆ መያዝ፣ጭንቀትን፣ስጋትንና ውጥረትን ለማስወገድና ከግማሽ በላይ የሚሆኑ በሽታዎችን ለመፈወስ አመርቂ ውጤት እንዳላቸው ስለሚገነዘቡ ነው። ዶክተር ኤ፣ኤ፣ብሬል ‹ሃይማኖተኛ ሰው በእርግጥ በስነልቦና በሽታ ፈጽሞ አይጠቃም› እስከማለት ደርሰዋል።››

ፈጣሪ ርህሩህ መሓሪና ቸር በመሆኑ፣የሰዎች መንፈስ ሕያው ሆኖ ሕይወታቸውን በሥርዓት ይመሩ ዘንድ ጃይማኖትን ደንግጎላቸዋል።አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ፣ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፤)››[አል አንፋል፡24]

በመሆኑም ተፈጥሮን በመጻረር የአላህን ሕልውና እንክዳለን የሚሉ ወገኖች እንኳ በውስጣቸው ውሸታቸውንና ክህደታቸውን ያውቃሉ። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በርሷ ካዱ፤የአመጸኞችም ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት።››[አልነምል፡14]

በጭንቅና በመከራ ሰዓት አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥመው ይህን በግልጽ ያያል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ብትመጣባችሁ፣ከአላህ ሌላን ትጠራላችሁን? እውነተኞች እንደ ኾናችሁ ንገሩኝ በላቸው። አይደለም እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ፤ቢሻም ወደርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግዳል፤የምታጋሩትንም ነገር ትተዋላችሁ (በላቸው)።››[አል አንዓም፡41-42]

በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ፣ጌታውን ወደርሱ ተመላሽ ኾኖ ይጠራል። ከዚያም ከርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደርሱ ይጸልይበት የነበረውን (መከራ) ይረሳል፤ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል፤በክሕደት ጥቂትን ተጣቀም፤አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ በለው።››[አል ዙመር፡8]

www.aroadtohappiness.com

ዴል ካርኒጄ

አሜሪካዊ ደራሲ
ጥልቅ ሁን
ፈላስፋው ፍራንሲስ ቢኮን ፦ ‹‹ጥቂቱ ፍልስፍና ሰውን ወደ ኤቲዝም ሲቀርብ፣የፍልስፍና ጥልቅ ዕውቀት ግን ወደ ሃይማኖት ይመልሰዋል›› ማለቱ በጣም ትክክል ነበር።

መላው የሰው ዘር አላህ በፈጠራቸው ንጹሕ ተፈጥሯቸው፣በጥቀምም ሆነ መጉዳት በእጁ የሆነውን፣ያሻውን የሚሰራና የፈለገውን የሚወስን የሆነውን አንድ አምላክ የማምለክ ባሕርይ ይዘው ተወልደዋል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አላህም በጉዳት ቢነካህ ለርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፤በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።››[አል አንዓም ፡14]

በተጨማሪምአላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታት ለርሷ ምንም አጋጅ የላትም፤የሚያግደውም ከርሱ በኋላ ለርሱ ምንም ለቃቂ የለም፤እርሱም አሸናፊው፣ጥበበኛው ነው።››[ፋጢር፡2]

የሰው ልጅ ሃይማኖትን ቢያጣ ኖሮስ?!

ሰው ሁለት ኃይሎች አሉት፤አንደኛው የዕውቀት ኃይል ሲሆን ሌላው የፍላጎት ኃይል ነው። ሁለቱን እውን ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት መጠንም ከፈለገው ግብ ይደርሳል። የመጀመሪያውን ማለትም የዕውቀትን ኃይል በተመለከተ፣ለአላህ ለስሞቹና ለባህርያቱ፣ለትእዛዛቱና ለእገዳዎቹ ግዴታ የሆነበትን በማወቁ ረገድ በሚኖረው ዕውቀት መጠን፣በተግባራዊ ስነምግባሩና በጸባዩ፣ወደ አላህ የቀረቡ ደጋግ አገልጋዮቹን መንገድ እንዴት እንደሚከተል፣በተጓዦቹየመወጣጫደረጃዎች ላይ እንዴት ከፍ እንደሚል፣ስለ ሰው ልጅ ነፍስያ ውስጣዊ ተፈጥሮ፣ስለ ደዌዎቿና ስለ ቆሻሻዎቿ፣እንዴት ሊረታትና ሊገራት እንደሚችል፣በጠላቶቿና እርሷን ከጌታዋ በሚያግዱት ሁሉ ላይ እንዴት ድል መቀዳጀት እንደሚቻል በሚኖረው እውቀት ደረጃ፤ወደ መጠቀ መንፈሳዊ ደረጃና ወደ ላቀ መንፈሳዊ ግብ በሚያደርሰው መልኩ ራሱን ከርካሽ ቁሳዊ ፍላጎቶችና የወረዱ ስሜታዊ ዝንባሌዎች በራቀ ሁኔታ በውብ ስነምግባርና በምስጉን ባሕርያት ከማነጽና ከመግራት ጎን ለጎን . . ለአላህ የሚኖረው ተገዥነትና ተመሪነት፣አላህ ዘንድ የሚኖረው ደረጃና ስፍራም፣የወዳኛው ሕይወት ተድላና በደስታ ብቻ ሳይሆን የዚች ዓለም ተድላና ደስታውም ጭምር በዚህ መጠን ይሆናል።

www.aroadtohappiness.com

ዶክተር ዳግላስ

የሪጂና ከንቲባ
ጉልሁ እውነታ
‹‹የዶክትሬት ዲግሪ ጥናቴ በስነትምሕርትና በአገር (nation) ግንባታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣መሠረታዊ የእስላም ማእዘናት አገርን በማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መንፈሳዊ ዘርፎች ዳግም ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥሉና ጠቃሚ መርህ የሚያቀርቡ መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁሉና።››

ይልቁንም ይህ የዕውቀት ኃይልና አቅም ከጽናትና ከቀጥተኝነት በተጨማሪ በውስጡ ባካተተው ቅን መመሪያ፣የፍላጎት ኃይል መጋቢና ስንቅ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ፣ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፤››[አል አንፋል፡24]

ይኸውና የኤቲዝም ጎራዎች የመንፈስ እርካታን ማስገኝት ቀርቶ የአካልን እርካታ ማስፈን ስለተሳናቸው ክስረታቸውን እያወጁ ነው። ያሻቸውን ያህል ብልጭልጭ የማታለያ ቃላቶቻቸውን እርስበርሳቸው ቢለዋጡና አሰማምረው ቢነዙ እውነተኛውን ደስተኝነት ለሰውልጆች ለማቅረብ ሳይችሉ መክነዋል።

www.aroadtohappiness.com

ዴል ካርኒጄ

አሜሪካዊ ደራሲ
ሃይማኖተኝነት ለበሽታዎች ፈውስ ነው
‹‹ጠንካራ እምነትና ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝ፣ጭንቀትን፣ ስጋትንና ውጥረትን ለማስወገድና እነዚህን በሽታዎች ለመፈወስ አመርቂ ውጤት እንዳላቸው የስነልቦና ሐኪሞች ይገነዘባሉ።››

የሰው ልጅ በአደጋና በመከራ ወቅት ወደማነው የሚማጸነውና የሚወተውተው?! ወደ ብርቱው ማእዘን ነው የሚጠጋው፤ኃይልና ተስፋ፣ክጀላና ትዕግስት፣በጎ መተማመንና ነገሮችን ሁሉ ለርሱ መስጠት ወዳለበት ወደ ኃያሉ አላህ ነው የሚሸሸው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹(እነሱም)እነዚያያመኑ፣ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፤ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ።››[አል ረዕድ፡28]

www.aroadtohappiness.com

ዊልያም ጄምስ

አሜሪካዊ የስነልቦና ሊቅ
ራስህን በራስህ ፈውስ
‹‹ለመንፈስ ጭንቀት ታላቁ ፈውስ በአላህ ማመን ነው።››

በግፍና በጭቆና እሳት ተለብልቦ ምሬት ሲሰማው ይህ ዩኒቨርስ ፈጣሪ ጌታ እንዳለው፣ቆይቶም ቢሆን ለጭቁን ተጎጂው ረድኤቱ እንደሚመጣ፣እያንዳንዱ ሰው እንደሥራው ዋጋውን የሚያገኝበትና በጎ የሠራም ሆነ ክፉ የሠራው ፍርዱን የሚያይበት የትንሣኤ ቀን ስለመኖሩ እርግጠኛ ይሆናል። በዚህም በአላህ (ሱ.ወ.) ላይ በሚኖረው መተማመንና እርግጠኝነት ልቡ ይረካል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹የአላህን ውዴታ የተከተለ ሰው፣ከአላህ በኾነ ቁጣ እንደ ተመለሰና መኖሪያው ገሀነም አንደ ኾነ ሰው ነውን? መመለሻውም ምን ይከፋ!››[ኣሊ ዒምራን፡162]

www.aroadtohappiness.com

ዐሊ ዕዘት ቢጎቢች

የቀድሞ የቦስኒያ ሄርዝጎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት
ሁለቱ ይለያያሉ
‹‹ቁሳዊነት ሁሌም የሚያረጋግጠው በእንስሳና በሰው መካከል የጋራ የሆነውን ነገር ሲሆን . . ሃይማኖት ግን በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ያረጋግጣል።››

የሰው ልጅ ሃይማኖትን ቢያጣ ኖሮስ?!

በተቃራኒው ደግሞ አላህን (ሱ.ወ.) ማወቅና በርሱ ማመንን ያጣ ሰው ሁሉንም ኃይል ያጣ፣የመንፈስ እርካታና ውስጣዊ መረጋጋትን፣ደስተኝነትም ተነፍጎ በጭንቀት በውጥረትና በሀዘን ማእበል ውስጥ የሚኖር ሰው ነው። የተረጋጋ አእምሮም ሆነ ውስጣዊ ሰላም የሌለው ሲሆን፣ብቸኛ ግቡ ሥጋዊ መደሰቻንና ስሜታዊ ፍላጎቶችን ለማርካት ገንዘብ ማሳደድ ነው። የሚኖርለት ዓላማም ሆነ የሕይወት ግብ የሌለው፣ ደስተኝነትን ፍለጋ ሲለፋና ሲባዝን የሚኖር፣የስጋዊ ፍላጎቶቹ ተገዥ ሆኖ የሚኖር በመሆኑ ከሰውነት እየወረደ ወደ አንስሳዊነት ብቻ ሳይሆን ከዚያም ወደ ከፋ ይዘቅጣል።አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ይልቁንም አብዛኞቻቸው የሚሰሙ፣ወይም የሚያውቁ፣መኾናቸውን ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም፣ከቶውንም እነሱ ይልቅ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው።››[አል ፉርቃን፡44]

www.aroadtohappiness.com

ሄንሪ ፎርድ

የአሜሪካው ፎርድ ኩባንያ መስራች
ሰባኪያን ሐኪሞች
‹‹የስነልቦና ሐኪሞች አዲስ ዓይነት ሰባኪያን እንጂ ሌላ አይደሉም። ሃይማኖትን አጥብቀን እንድንይዝ የሚጎተጉቱን የወዲያኛውን ዓለም የገሀነም ቅጣት በመስጋት ሳይሆን፣ ሃይማኖትን እንድንይዝ የሚመክሩን የዚችን ዓለማዊ ሕይወት ሲኦል፣ከየጨጓራ ቁስልን፣የስነልቦና መናድንና የእብደትን ገሀነም በመስጋት ነው።››

ስቃይና መከራ ስለወረረው የስነልቦና ውድመትና የውስጣዊ ጭንቀት ሰለባ ይሆናል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከግሣጼም የዞረ ሰው፣ለርሱ ጠባብ ኑሮ አልለው፤በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን።››[ጣሃ፡124]

www.aroadtohappiness.com

አርኖልድ ቱዌይንቢ

እንግሊዛዊ ታሪክ ጸሐፊ
ሃይማኖት ሕይወት ነው
‹‹ሃይማኖት ወሳኝ ከሆኑ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ተሰጥኦዎች አንዱ ነው። የሃይማኖት እጦት አንድን ሰው፣ምኑም የራሱ ካልሆነ ገበታ ላይ ሃይማኖታዊ ማጽናኛ ፍለጋ ለመሄድ ወደሚያስገድደው የተስፋ መቁረጥና የመንፈስ ዝቅጠት ሁኔታ ያስገባዋል።››

ጌታው ያወቀ፣ኃያልነቱን የተገነዘበ፣ለርሱ መፈጸም የሚገባቸውን ግዴታዎችም የተረዳ፤ሸሪዓውን በመከተል ለትእዛዛቱ ታዛዥ በመሆንና ከእገዳዎቹ በመከልከል የርሱን ውዴታ ለማግኘት የጓጓ፤ጌታው በትንሹም በትልቁም፣በግልጹና በስውሩም፣በሁሉም ጊዜና ስፍራም ለርሱ ወሳኝና የዘውትር አስፈላጊው መሆኑን ያወቀ ሰው ይህን ሁሉ ከማያውቀው ሰው የተለየ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እላንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።››[ፋጢር፡15]

www.aroadtohappiness.com

ሬይኔ ዶሎ

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ደራሲ
ዘመነ ጭንቀት
‹‹ዛሬ የምንኖረው በዘመነ ጭንቀት ነው፤የሳይንስና የቴክኖሎጂ ስኬቶች ለሰው ልጅ እድገትና ብልጽግናን መጨመራቸው እሙን። ይሁን እንጂ ደስተኝነትንና ውስጣዊ እርካታን አልጨመሩለትም። በተጻራሪው ጭንቀትን፣ተስፋ መቁረጥንና በሕይወቱ ውስጥ ያለውን ውብ ትርጉም ያሳጡትን የስነልቦና በሽታዎችን ነው የጨመሩለት።››

ልቡ በጥርጣሬና በግራመጋባት ተሞልቶ እርግጠኝነትን ማጣትና ባዶ ግምቶች ወደ መከፋትና ተስፋ መቁረጥ ጨለማ የወሰዱት ሰው፣ዓለማዊ መደሰቻዎችንና ጊዜያዊ ማርኪያዎችን ቢያገኝም፣ከፍተኛ ሹመትና ማእረግ ማግኘት ቢሳካለትም እንኳ እውነተኛ ደስተኝነትንና ውስጣዊ እርካታን የማግኘት ጥረቱ ከንቱ ይሆናል። አላህን ለማግኘት ያልታደለ ምን አግኝቶ?! አላህን ያገኘ ምን አጥቶ?!

  - ከደስተኝነት ውይይቶች ጋር የተያያዙ
  - ከልቦለዱ ጋር የተያያዙ
  - ከመጽሐፎች ጋር የተያያዙ
  - ከምስል ጋር የተያያዙ