face

ሃይማኖት ለሕብረተሰቦች ያለው አስፈላጊነት

ሃይማኖት ለሕብረተሰቦች ያለው አስፈላጊነት

ሃይማኖት ለሕብረተሰቦች ያለው አስፈላጊነት

ሃይማኖት ለሕብረተሰቦች ምን ያህል አስፈላጊ ነው?? . .

www.aroadtohappiness.com

አርነስት ሬናን

ፈረንሳዊ ታሪክ ጸሐፊ
አፍ አውጥቶ የሚናገር ማስረጃ
‹‹የምንወደው ማንኛውም ነገር መመንመኑ፣አእምሮን ሳይንስንና እንዱስትሪን የመጠቀም ነጻነትም ሊከሽፍ ይችላል። ሃይማኖተኝነት ግን ፈጽሞ ሊከስም አይችልም። ይልቁንም ሰውን በምድራዊ ሕይወት ወራዳ ጠባብ መተላለፊያዎች ውስጥ ብቻ ወስኖ ለማስቀረት የሚፈልገው የቁሳዊነት አመለካካት ውድቅ መጎኑን ጮሆ የሚናገር ማስረጃ እንደሆነ ይቀጥላል።››

ሃይማኖት ለግለሰብ ወሳኝ አስፈላጊ ከሆነ ዘንዳ ለሕብረተሰቦች የሚኖረው አስፈላጊነት ይበልጥ የጸና ይሆናል። የሰው ልጆች ሕይወት በመካከላቸው በሚኖረው በበጎ ነገሮች ላይ የመረዳዳትና የመተባበር መሰረት ላይ እንጂ የማይታነጽ በመሆኑ፣ሃይማኖት ለአንድ ሕብረተሰብ የመከላከያ ጋሻ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፤ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ።››[አል ማእዳህ፡2]

www.aroadtohappiness.com

ፊሊፕ ሃቴይ

ሊባኖሳዊ ታሪክ ጸሐፊ
እውነተኛው ሕግ
‹‹እስላማዊው ሸሪዓ (ሕግ) ሃይማኖታዊውንና ዓለማዊውን ለያይቶ የማይመለከት ሲሆን፣የሰው ልጅ ከአላህ ጋር ያሚኖሩትን ግንኙነቶች፣ለአላህ ያለበትን ግዴታዎች በመደንገግ ያደራጃል። የሰው ልጅ ከመሰል ሰብአዊ ወንድሙ ጋር የሚኖሩትን ግንኙነቶችም እንዲሁ ይደነግጋል። ከሃማኖታዊ ዓለማዊና ሌሎችም ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ሁሉም የአላህ ትእዛዛትና እገዳዎች ቁርኣን ውስጥ ሰፍረዋል። ቁርኣን ውስጥ ከስድስት ሺ አንቀጾች በላይ ሲኖሩ አንድ ሺ ያህሎቹ ድንጋጌዎችን የሚመለከቱ ናቸው።››

ይህ ተራድኦና ትብብር ሊኖር የሚችለው ደግሞ ግንኙነቶቻቸውን በሚያደራጅ፣ግዴታዎቻቸውን በሚወስንና ለመብቶቻቸው ዋስትና በሚሰጥ ሥርዓት አማካይነት ብቻ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ሥርዓትም የግዴታ ውስጠ ዐዋቂና ጥበበ ረቂቅ በመሆኑ ከማንም በላይ ለፈጠራቸው ፍጡራን የሚበጀውን ከሚያውቀው ኃያል አምላክ ዘንድ የመጣ መሆን ይኖርበታል። ‹‹የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ውስጥ አዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን።››[አል ሙልክ፡14]

www.aroadtohappiness.com

ቶማስ አርኖልድ

እንግሊዛዊ ኦሪየነታሊስት
ለስሜታዊ ዝንባሌዎች ቦታ የሌለው ሃይማኖት
‹‹ሙሐመድ በመዲና ላገኙት ሞቅ ያለ አቀባበል ምክንያት ከሆኑት ውስጥ፣ለሊሂቃኑ መደብ የመዲና ነዋሪዎች ወደ እስላም መግባት የማህበረሰቡ ችግር ሆኖ ለቆየው ለዚያ ሥርዓተ አልበኝነት መፍትሔ ሆኖ መታየቱ አንዱ ነው። ይህም በእስላም ውስጥ ባገኙት ጥብቅ የአነዋነዋር ሥርዓትና የሰዎችን ልቅና አፈንጋጭ ስሜታዊ ዝንባሌዎች ከግለሰባዊ ዝንባሌዎች በላይ ከሆነው ሥልጣን ለተደነገጉ ሕጎች ተገዥ በማድረግ አቅሙ ነው።››

የሰው ልጆች ከሃይማኖት ከሕግጋቱና ከሥርዓቱ ባፈነገጡ ልክ፣በጥርጣሬ፣ በጥመት፣ በብክነት፣በመባዘን፣ግራ በመጋባት፣ በመናጢነትና በመላየለሽነት ጨለማ ውስጥ ይዋጣሉ።

የሃይማኖተኝነት ጥንካሬ በሕብረተሰብ ትስስርና መረጋጋት ላይ ያለው ተጽእኖ

በሕብረተሱቡ ውስጥ አንድነትን ሰላምንና መረጋጋትን ለማስፈን፣ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ከሃይማኖት ኃይል ጋር የሚነጻጸር ወይም የሚቀርበው ምንም ዓይነት ሌላ ኃይል በዓለም ላይ የለም። የዚህ ምስጢር ደግሞ የሰው ልጅ እንቅስቃሴዎቹና ድርጊቶቹ በራሱ ምርጫ የሚፈጸሙና በማይታይና በማይጨበጥ ነገር የሚመሩ በመሆናቸው ከተቀሩት ሕያው ፍጥረታት ሁሉ የተለየ ነው። እንቅስቃሴዎቹና ድርጊቶቹ የሚመሩት መንፈሱን በሚያጠራ፣ ጸባይና ስነምግባሩን በሚገራ፣ግልጹን አካላዊ እንቅስቃሴውን እንደሚቆጣጠረው ሁሉ ስውሩን ውስጣዊ ሕሊናዊ ሁኔታውንም በሚቆጣጠረው ሃይማኖታዊ እምነት ነው። ‹‹በንግግር ብትጮኽ፣(አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው)፤እርሱ ምስጢርን፣በጣም የተደበቀንም ያውቃልና።››[ጣሃ፡7]

የሰው ልጅ ትክክለኛም ይሁን የተሳሳተ የሚመራው ሁሌም በእምነት (በዐቂዳ) ነው። ዐቂዳውጥሩና ትክክለኛ ከሆነ ነገሩ ሁሉ መልካም ይሆንለታል፤መጥፎና የተሳሳተ ከሆነ ደግሞ ነገሩ ሁሉ የተበላሸ ይሆናል።

በመሆኑም ሃይማኖት በሰዎች መካከል በይነሰባዊ ግንኙነቶች በፍትሕና ርትእ መሠረቶች ላይ የታነጹ እንዲሆኑ የሚያደርግ አስተማማኝ ዋስትና ነው። በዚህ ምክንያትም ሃይማኖት ማሕበረሰባዊ ግዴታ በመሆኑ በሕዝቦች መካከል የሚይዘው ስፍራ ልብ በሰው አካል ውስጥ የሚይዘው ስፍራ መሆኑ አስደናቂ አይሆንም።

www.aroadtohappiness.com

ቮልተር

ፈረንሳዊ ፈላስፋ
አእምሯችሁ የት ሄደ?!
‹‹በአላህ መኖር ለምንድነው የምትጠራጠሩት?! እርሱ ባይኖር ኖሮ ባቤቴ ክህደት በፈጸመችብኝ፣አገልጋዬም በሰረቀን ነበር።››

ሃይማኖት በአጠቃላይ መልኩ ይህን የመሰለ ደረጃ የያዘ ሲሆን፣ዛሬ በዓለም ላይ የምናስተውለው ግን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣እምነቶችና ጎራዎች መኖራቸውን ነው። የእያንዳንዱ እምነትና ጎራ ተከታዮችም በእምነታቸው ደስተኞች ሆነው የሙጥኝ መያዛቸውን እንመለከታለን። ታድያ የሰው ልጅ የሚጓጓለትን ግብ እውን የሚያደርግለት እውነተኛው ሃይማኖት የትኛው ይሆን?! የእውነተኛ ሃይማኖት መመዘኛዎችስ ምንድናቸው?!

  - ከደስተኝነት ውይይቶች ጋር የተያያዙ
  - ከልቦለዱ ጋር የተያያዙ
  - ከመጽሐፎች ጋር የተያያዙ
  - ከምስል ጋር የተያያዙ