face

ከሃይማኖቶች የእውነተኛ ሃይማኖት መመዘኛዎችን የሚያሟላው የትኛው ሃይማኖት ነው?

ከሃይማኖቶች  የእውነተኛ ሃይማኖት መመዘኛዎችን የሚያሟላው የትኛው ሃይማኖት ነው?

ከሃይማኖቶች የእውነተኛ ሃይማኖት መመዘኛዎችን የሚያሟላው የትኛው ሃይማኖት ነው?

የሃይማኖቶች ምደባ

አላህ ግን አንድ ነው
‹‹በምድራዊ ሃይማኖቶች ውስጥ ያሉትን አማልክት ብዛት መቁጠር ለተመራማሪዎች አድካሚ ሆኗል። የጥንት ግብጻውያን አማልክት ቁጥር ከ800 በላይ ነው። የሂንዱዎች አማልክት ብዛት ከ10000 በላይ ነው። በግሪኮች በቡድሂስቶችና በተቀሩት የምድራዊ ሃይማኖቶች ተከታዮች ዘንድም ይህንኑ ዓይነት ጣዖታዊነት እናስተውላለን።››

በምንጫው መሠረት ሃይማኖቶችን በሁለት መደብ መክፈል ይቻላል፦

ሰዎች የሚወስኗቸና የሚያሻሽሏቸው፣ከአላህ (ሱ.ወ.) ያልተላለፉ መለኮታዊ ያልሆኑ ምድራዊ ሰው ሠራሽ ሃይማኖቶች። እነዚህ እንደ ቡድሂዝም ሐሕንዱ ዞሪስቴሪያንና ጣዖታዊነት ያሉ እምነቶች ሲሆኑ፣አምነታቸው ከግላዊ ዝንባሌዎቻቸው የሚመነጭና ከእውነተኛው ሃይማኖት ፈጽሞ የራቀ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣በዓይኑም ላይ ሽፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ ኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን?››[አል ጃሢያ፡23]

እንዲህ ዓይነቱ እምነት የሰው ልጅ ስሜታዊ ዝንባሌ የፈጠረው እንጂ ፈጽሞ መለኮታዊ ሃይማኖት አይደለም። ሰው ሠራሽ ሃይማኖቶች በአፈተረቶች፣በቅዠት ሀሳቦች፣በመደብ በደልና ጭቆና እና በቅራኔዎች የታጨቁ ናቸው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ፣በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር።››[አል ኒሳእ፡82]

www.aroadtohappiness.com

ቶሊስቶይ

ሩሲያዊ የስነጽሑፍ ሰው
እውነተኛው ሕግ
‹‹ገብቶኛል . . ተረድቼአለሁ . . ለሰው ልጅ አስፈላጊው ነገር እውነትን የሚያረጋግጥ፣ሐሰትን የሚያስወግድ መለኮታዊ ሕግ ነው።››

ከአላህ (ሱ.ወ.) ዘንድ የተላለፉ እንደ አይሁዳዊነት ክርስትና እና እስላም ያሉ መለኮታዊ ሃይማኖቶች። ለነዚህ ሃይማኖቶች ተከታዮች ፈጣሪ አምላክ ሃይማኖታቸውን ደንግጎላቸው መርጦላቸዋል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ለናንተ ከሃይማኖት ያንን ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን፣ያንንም በርሱ ኢብራሂምን፣ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን፣ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ፣በርሱም አትለያዩ፣ማለትን (ደነገግን) በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፤አላህ የሚሻውን ሰው ወደርሱ (እምነት) ይመርጣል፤የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል።››[አል ሹራ፡13]

የሰው ሠራሽ ሃይማኖቶች ባሕርያት

ሰው ሠራሽ ምድራዊ ሃይማኖቶች ከደንጋጊዎቻቸው ስሜታዊ ዝንባሌዎች ጋር የሚጣጣሙና ከአጭር ጊዜ በኋላ ሰዎች አይረቤነታቸውን በመረዳት በየጊዜው ለማሻሳልና ለመለዋወጥ የሚሞክሯቸውን ዝርዝር ሀሳቦችና አቋሞችን ያካተተ ግዙፍ ስብስብ መሆናቸው ጥርጥር የለውም። እነዚህ ምድራዊ ሕጎች ካሏቸው በርካታ መለያ ባሕርያት መካከል የሚከተሉትን እናገኛለን፦

በአላህ ማጋራት (ሽርክ) ፦ በየዕለቱ የሚያመልኩባቸውን አዳዲስ አማልክት ያመርታሉ፤አማልክቶቻቸው የራሳቸው እጅ ሥራ ውጤቶች ናቸው። ከኃያሉ አላህ ጋር ባእድ አማልክት ፈጽሞ መኖር እንደማይችሉ አያስተውሉም ወይም አያስተነትኑም። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፤ከርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፤ያን ጊዜ፣(ሌላ አምላክ በነበረ)፣አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፤ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፤አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ። ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፤(በርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ።››[አል ሙእሚኑን፡91-92]

ግፈኛው የመደብ ክፍፍል
‹‹የሕንዱ መደባዊ ክፍፍል እንዲከተለው የተደለደለ ነው፦ የነጮች መደብ፣ይህ የሃይማኖት መሪዎችንና አዋቂዎችን የያዘ ነው። የቀያዮች መደብ፣ይህ ደግሞ መሳፍንቱንና ፈረሰኞችን ያቀፈ ነው።የብጫዎች መደብ፣ይህ ገበሬዎችንንና ነጋዴዎችን ያቀፈ ነው። የጠቋቁሮች መደብ፣ ይህ ደግሞ የሞያና የእደጥበብ ሠራተኞችን ያጠቃለለ ነው። አምስተናው መደብ ወይም የእርኩሳን መደብ በመባል የሚታወቀው ደግሞ በተቀሩት የተናቁ ሥራዎች ላይ የተሰማሩትን ሁሉ ያካትታል። የላይኞቹ መደቦች በታችኞቹ መደቦች ላይ የጌትነት ሥልጣን ሲኖራቸው፣የታችኞቹ መደቦች ደግሞ ለላይኞቹ መደቦች አገልጋይ የመሆን ግዴታ አለባቸው።››

ማሕበራዊ የመደብ ጭቆና ፦ መልኮታዊ ያልሆኑ ሃይማኖቶች ደንጋጊዎቹ ለራሳቸው፣ ለቡድናቸው መደብና ለሚፈልጓቸው መደቦች ከሌሎች የተለየ ልዩ መብቶች ይሰጧቸዋል። ይህም ፍላጎታቸውን ለማርካትና ሌሎችን የነሱ መብት አልባ አገልጋዮች ለማድረግ ዓላማ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እላንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤እንድትተዋወቁም ጎሣዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤አላህ ዘንድ በላጫችሁ፣በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤አላህ ግልጽን ዐዋቂ፣ውስጥንም ዐዋቂ ነው።››[አል ሑጁራት፡13]

አላህ (ሱ.ወ.) ሌሎችን በንቀት ዓይን መመልከትንና በማንም ቢሆን መሳለቅን ከልክሏል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፤ከነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፤ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፤ከነሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፤››[አል ሑጁራት፡11]

ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ.) ዘንድ ነጩ በጥቁሩ ላይ፣አንዱ ጎሳ በሌላው ጎሳ ላይ፣አንዱ ሕዝብ በሌላው ሕዝብ ላይ ምንም ዓይነት ብልጫ የለውም። በተቃራኒው ግን ከነዚህ ምድራዊ ሃይማኖቶች ብዙዎቹ በአስከፊ የመደብ አድልዖና ጭቆና ላይ የታነጹ ናቸው።

የሰውን ተፈትሮ መጻረር ፦ ምድራዊ ሰው ሠራሽ ሃይማኖቶች የሰውን ተፈጥሮ በመጻረር የማይችለውንና የማገባውን በማሸከም ላይ የተመሰረቱ፣ሰብአዊ ተፈጥሮንና ጤናማ አእምሮን በመቃረን የቆሙ፣ተከታዮቻቸው ከቀጥተኛው መንገድ ርቀው ያፈነገጡ ናቸው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህ ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፤የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃማኖት ያዙዋት)፤የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፤ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፤ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።››[አል ሩም፡30]

አፈተረቶችና የቅዠት ሀሳቦች ፦ እነዚህ ምንም ዓይነት አእምሯዊ ሎጂካዊም ሆነ ሳይንሳዊ መነሻ ሳይኖራቸው በባዶ ቅዠት ላይ የተመሰረቱ እምነቶች ወይም አስተሳሰቦች ናቸው። ምድራዊ ሃይማኖቶች አንዳች ማስረጃም ሆነ መሰረት በሌላቸው ተራ የቅዠት ሀሳቦች የተሞሉ ሲሆን በቅዠት ላ ሊመሰረት የሚችለው ቅዠት ብቻ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እውነተኞች እንደኾናችሁ አስረጃችሁን አምጡ፣በላቸው።››[አል ነምል፡64]

የቡድሂዝም መጣረስ
‹‹ቡድሂስቶች ወይም ከፊሎቻቸው የአምላክን መኖር ሲያስተባብሉ፣ቡድሃን የአምላክ ልጅ ነው ይላሉ። መንፈስ መኖሩንም ሲያስተባብሉ የሙታን ነፍስ በሌላ ፍጡር አካል ትመለሳለች ብለው ያምናሉ። ››

እርስ በርሳቸው መጣረስ ፦ ሰው ሠራሽ እምነቶች በቅራኔዎች የተሞሉ፣እያንዳንዱ ቡድን ከተቃረነውና ከአብራኩ ወጥቶ በተሸሻለው ሌላው ቡድን ውድመትና ፍርስራሽ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ፣በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር።››[አል ኒሳእ፡82]

የመለኮታዊ ሃይማኖቶች ተልእኮ

መለኮታዊ ሃይማኖቶች ግን፣የአላህን ቃልና መልክቱን ያደርሱ ዘንድ መልክተኞችን በመላክ ሊመራቸውና መንገዱን ሊያበራላቸው፣ከከንቱነትና ከመዋለል፣ከአፈተረትና ከማጋራት፣የሰውን ተፈጥሮና ሰብአዊ አእምሮን ከመጻረር ሊያርቃቸው ከአላህ ለሰው ልጆች የተቸሩ ጸጋዎቹ ናቸው። ‹‹ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅእንዳይኖር፣አብሳሪዎችና እስፈራሪዎች የኾኑን መልክተኞች (ላክን)፤አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።››[አል ኒሳእ፡165]

  - ከደስተኝነት ውይይቶች ጋር የተያያዙ
  - ከልቦለዱ ጋር የተያያዙ
  - ከመጽሐፎች ጋር የተያያዙ
  - ከምስል ጋር የተያያዙ